ከPicasa በመቀጠል ላይ
በGoogle ፎቶዎች ውስጥ በአንዲት የፎቶ አገልግሎት ላይ እንድናተኩር Picasaን ለማቋረጥ ወስነናል – በመላ ሞባይል እና ድር ላይ ያለውጣ ውረድ የሚሰራ አዲስ፣ ዘመናዊ የፎቶ መተግበሪያ።
የት ነው ፎቶዎቼን ማግኘት የምችለው?

በአንድ የPicasa ድር አልበም ውስጥ ፎቶዎች ወይም ቪዲዮዎች ካለዎት አብዛኛውን ይዘት አሁንም መድረስ፣ መቀየር እና ማጋራት የሚችሉበት ቀላሉ መንገድ ወደ Google ፎቶዎች መግባት ነው። የእርስዎ ፎቶዎች እና ቪዲዮዎች አስቀድመው እዚያ ይሆናሉ።

ወደ Google ፎቶዎች ይሂዱ
አሁንም ዴስክቶፕ መተግበሪያውን መጠቀም እችላለሁ?

አስቀድመው ላወረዱ ሰዎች ልክ ዛሬ እንደሚሰራው ሁሉ መስራቱን ይቀጥላል። ነገር ግን ከዚህ ባሻገር አናዳብረውም፣ እና ለወደፊቱ ምንም ዝማኔዎች አይኖሩም።

ወደ Google ፎቶዎች ለመቀየር ከመረጡ የዴስክቶፕ መስቀያውን ተጠቅመው ፎቶዎችን እና ቪዲዮዎችን photos.google.com/apps ላይ መስቀሉን መቀጠል ይችላሉ።

ተጨማሪ ለመረዳት